Featured Image
በኢትዮጵየ የወንጌላዊያን ነጋዴዎች ኔትወርክ (EBN ETHIOPIA) በየ2 ወሩ የሚደረገው የ#HEAVEN_ON_BUSINESS መርሀግብር በዚህኛው ዙር ከወትሮው በተለየ "ሀገር አቀፍ ልዩ የስልጠና ፕሮግራም" ከThe Generosity Path እና Salvation Voice Ministries ጋር በአጋርነት ቅዳሜ ፣ጥቅምት 9፣2018 ሙሉ ቀን በስካይ ላይት ለ250 ነጋዴዎች ተከናውኗል።
የፕሮግራሙ ዋና ሀሳብ "መፅሀፍ ቅዱሳዊ የልግስና ጉዞ" "The Journey of Generosity" በሚል ሲሆን ወንጌላዊያን ነጋዴዎች ንግድን ለትርፍ ብቻ ከመጠቀም ባለፈ በዙሪያችን ላለው የማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጥ እንዲሆን ልምድን ለማካፈል የተዘጋጀ ነው።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ከሀዋሳ፣ ከሻሸመኔ ፣ከሆሳእና ፣ከዱራሜ ፣ከወላይታ ሶዶ፣ከደብረዘይት፣ከሀረር እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን ፣ከኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ በንግድ ስራ የተሰማሩ ወንጌላዊያን ልምዳቸውን ለማካፈል ተገኝተዋል።
ይህ ስልጠና በቀጣይ በተለያዩ ከተሞች የሚቀጥሉ ሲሆን ንግድን ለተልእኮ ለወንጌል አላማ በመጠቀም ሀገር አቀፍ ንቅናቄን የምንፈጥር ይሆናል።
ይህ ፕሮገራም እንዲሳካ በአጋርነት አብረውን ያገለገሉትን ተቋማት በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን !
15 Views
2 Saves